አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ቢሮ ጋር በመሆን በሀገሪቱ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ የሚፈልጉ ዳያስፖራ ባለሀብቶችን የሚያበረታታ እና ግንዛቤ የሚያሳድግ ፎረም አዘጋጁ።
ሁለቱ ተቋማት በጋራ በሠጡት መግለጫ ፎረሙ ጥር 3 ስራ የሚጀምር ሲሆን፥ ጥር 6 ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡
ፎረሙ ጥር 3 በይፋዊ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እንደሚጀመር እና በቀጣይ ቀናትም የተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚኖሩት ነው ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፥ ኢትዮጵያ ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን የማፍሰስ ዕቅድ ያላቸው ዳያስፖራ ባለሐብቶች በፎረሙ እንዲሳተፉ እና ከኢንቨስትመንት ማኅበረሰቡ፣ ከኮሚሽኑ የፌዴራል እና የክልል እንዲሁም የከተማ አሥተዳደር ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር እንዲመክሩ ብሎም የኢንቨስትመንት አማራጮችን እንዲመለከቱ ነው ጥሪ ያቀረበው፡፡
በኢንቨስትመንት መሰማራት እና በዕድሉ መጠቀም የሚፈልጉ ባለሐብቶች investethio.com የሚለውን የኮሚሽኑን ድረ ገጽ መመልከት እንደሚችሉም ተጠቁሟል፡፡
የልምድ ልውውጥ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ጉብኝት እንደሚኖር የተገለጸ ሲሆን÷ ይህም ዳያሰፖራው በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጭ እና አቅሙን እንዲያውቅ እና መዋዕለ ንዋዩን እንዲያፈስ ያስችለዋል ተብሏል፡፡
ዳያስፖራው በሚያገኛቸው አጋጣሚዎችም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት አምባሳደር ሆኖ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያስተዋውቅ ግንዛቤ የሚሰጥ ጉብኝት እንደሚሆን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ገልጸዋል።
በፎረሙ ሰባት የሚደርሱ ሚኒስትር መሥሪያ ቤቶችያሏቸውን የኢንቨስትመንት አማራጮች እንደሚያቀርቡም ተመላክቷል።
Via: FBC
UPCOMING EVENTS
No event found!