Home » “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” የመጀመሪያ ምዕራፍ መርሃ ግብሮች ይፋ ሆኑ

“ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” የመጀመሪያ ምዕራፍ መርሃ ግብሮች ይፋ ሆኑ

by Ethiopian Homecoming

“ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” የመጀመሪያ ምዕራፍ መርሃ ግብሮች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 3፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” ጥሪን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሀገር ቤት በሚቆዩባቸው ጊዜያት የሚሳተፉባቸው መርሃ ግብሮች ይፋ ተደርገዋል፡፡

መርሃ ግብሮቹ በሁለት ምዕራፍ የተከፈሉ ሲሆን÷ የመጀመሪያው ዙር ከሚያዚያ 3 እስከ ግንቦት 3፣ 2014 ዓ.ም እንዲሁም የሁለተኛው ዙር ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 4፣ 2014 ዓ.ም እንደሚቆይ ከዳያስፖራ ኤጀንሲ ያገነኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህ መሰረትም ከሚያዝያ 3 እስከ ግንቦት 3 ቀን 2014 ዓ.ም በኤርፖርት አቀባበል፣ ሚያዚያ 19 ቀን በወዳጅነት አደባባይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ስነ ስርዓት፣ ሚያዚያ 21 ቀን ታላቁ የጎዳ ላይ ኢፍጣር በመስቀል አደባባይ እና ሌሎች መርሃ ግብሮች የሚከናወኑ ይሆናል፡፡

ዳያስፖራ ኤጀንሲ ለመጀመሪያው ዙር ይፋ ያደረጋቸው አጠቃላይ መርሃ ግብሮችም እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

eid to eid ethiopian homecoming

 

You may also like