Home » ወደ አገር ለሚገቡ የዳያስፖራ አባላት የተዘጋጁ ሁነቶች ይፋ ሆኑ

ወደ አገር ለሚገቡ የዳያስፖራ አባላት የተዘጋጁ ሁነቶች ይፋ ሆኑ

by Ethiopian Homecoming
ወደ አገር ለሚገቡ የዳያስፖራ አባላት የተዘጋጁ ሁነቶች ይፋ ሆኑ
ታህሳስ 18 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አንድ ሚሊዮን ዳያስፖራ ወደ አገር ቤት በሚል ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ የዳያስፖራ አባላት የተዘጋጁ የተለያዩ ሁነቶች ይፋ ሆኑ።
ethiopian homecoming events
የሚመጡ እንግዶች አቀባበልና መስተንግዶ ለማስተባበር የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ የተደረገውን ዝግጅት በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።
ወደ አገራቸው የሚመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆችን ለመቀበል ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን የተዘጋጁ ሁነቶችን ኮሚቴው ይፋ አድርጋል።
በዚህም መሰረት ታህሳስ 20 ቀን የመክፈቻ መርሀ ግብር ይካሄዳል።
ታህሳስ 24 ቀን ደግሞ በአዲስ አበባ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ጉብኝት፣ ከታህሳስ 25 እስከ 27 በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ጉብኝት ማካሄድና ሌሎች መርሀ ግብሮችም ይፋ ተደርገዋል።
ዳያስፓራው አገርን መልሶ ለመገንባት ሊያደርገው በሚችለው አስተዋፅኦ፣ ኢንቨስትመንትና ሌሎች ሲፖዚየሞችም በመርሀ ግብሩ ተካተዋል።
የሚካሄዱት ሁነቶች የሚካሄዱበት ቀን እንደ አስፈላጊቱ ሊከለስ እንደሚችልም ተጠቁሟል።
Monthly Weekly Daily List Grid Tile
No event found!

You may also like